ደቡብ ክልል ውስጥ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰው እርዳታ ይጠብቃል

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ ክልል ውስጥ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰው እርዳታ ይጠብቃል

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ድርቅ አብዛኛው የወረዳው ነዋሪዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውንና ከብቶቻቸውም እየሞቱባቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከድርቁ በተጨማሪ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም አለመኖሩ ጉዳት እንዳባባሰውና በቂ እርዳታም እንዳልደረሳቸው አመልክተዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ140 ሺህ በላይ ሰው በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የወረዳው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።

ደርቁን አስመልክቶ ከደቡብ ክልል ምክር ቤት ጋር መወያየታቸውን ለክልሉ መንግሥት ቴሌቪዥን የገለፁት የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ በክልሉ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰው የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡