"የተባበር በርታ መኖሪያ መንደር" ክፍለ ከተማውን በአጥፊነት ከሠሠ

  • መለስካቸው አምሃ
ፎቶ ፋይል፦ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና መቀመጫን የሚያሳይ

ፎቶ ፋይል፦ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና መቀመጫን የሚያሳይ

"የተባበር በርታ መኖሪያ መንደር"ን የግንብ አጥር፣ ክፍለ ከተማው በኀይል እና በድንገት እንዳፈረሰው ማኅበሩ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የተባበር በርታ ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ሥራ ማኅበር ነዋሪዎች፣ በክፍለ ከተማው ወረዳ ሦስት አስተዳደር፣ መብታቸው መጣሱን የማኅበሩ መሪ አስታውቀዋል።

የማኅበሩ መሪ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራች እና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ፣ “ንብረታችን አላግባብ ተነክቷል፤ ንብረታችን ፈርሷል፤” በማለት አስተዳደሩን በአጥፊነት ከሠዋል።

የወረዳው ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ርምጃውን እንዲወስድ ከበላይ አካል እንደታዘዘ በመግለጽ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመኾኑ ዝርዝር መረጃ አልሰጥም፤ ብሏል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

"የተባበር በርታ መኖሪያ መንደር" ክፍለ ከተማውን በአጥፊነት ከሠሠ