በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ በተከሠተው ድርቅ፣ የወረዳው አርብቶ አደሮች ለምግብ እጥረት እንደ ተዳረጉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በመኖ እጥረት ሳቢያ ከብቶቻቸውም እያለቁባቸው መኾኑን አክለው ገልጸዋል። የድርቁን አስከፊነት ያገናዘበ በቂ እርዳታ አይደርሰንም፤ ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ብዙ ሺሕ አርብቶ አደሮች፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ የሚሹ እንደኾኑና ቁጥራቸው የበዛ ከብቶች በድርቁ እንዳለቁ የወረዳው አስተዳዳሪና ባለሥልጣናትም አረጋግጠዋል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡