የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ የአልማዝ ምርት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማውጣት ማውረድ ይዟል

Your browser doesn’t support HTML5

የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ የአልማዝ ምርት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማውጣት ማውረድ ይዟል

የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበትን የመሪጀመሪያ ዓመት በሞስኮ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን በመጣል በያዘው ዕቅድ እያሰበ ነው። ቀደም ደም ሲል በሕብረቱ የተጣሉት ማዕቀቦች የነዳጅ ዘይት፣ ጋዝ፣

የድንጋይ ከሰል፣ ብረታብረት፣ ሲጋራ፣ ቮድካ እና ወርቅ በመሳሰሉት የሩሲያ ምርቶች ላይ የተነጣጠሩ ነበሩ።

የአሁኑ የሕብረቱ ማዕቀብ ዝርዝር ደግሞ ሩሲያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች አንዱና ዋነኛ የአልማዝ ምርቷን ያካትታል ተብሎ ተጠብቋል።

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ሊዛ ብራያንት የአልማዝ ማእድን ምርቷ ለአዲሱ የሕብረቱ ዕቅድ ትኩረት ምክኒያት የሆነበትን ለማወቅ የዓለም የአልማዝ ንግድ መናሃሪያ ወደሆነችው የቤልጅጓ አንትወርፕ አቅንታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።