የናይጄሪያ ፍርድ ቤት በመጭው ቅዳሜ የካቲት 18/2015 በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሀገር ውጭ ያሉ ዳያስፖራ መራጮች እንዲሳተፉ የሚጠይቀውን ክስ ውድቅ አድርጎታል።
ውሳኔው ከአገር ውጭ የሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን የዴሞክራሲ መብታቸውን መጠቀም ከፈለጉ ወደ ሀገራቸው መመለስ ያለባቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ናይጄሪያውያን የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ለመደገፍ በዓመት ቢሊዮኖች ዶላሮችን በኋላ ወደ ሀገራቸው የሚልኩ ሲሆን፣ ደጋፊዎችም ድምጽ መስጠት እንዲችሉ ሕገመንግሥቱ መሻሻል ይኖርበታል ይላሉ።
ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ ያደረገው ‘ናይጄሪያ ውስጥ የሚኖሩ የተመዘገቡ መራጮች ብቻ የመምረጥ መብት እንዳላቸው የሚናገረውን ሕገመንግሥት በመጥቀስ ነው።
እንግሊዝ አገር በሚኖሩ ሁለት ናይጄሪያውያን የቀረበው ክስ ቅዳሜ የካቲት 18 የሚካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዳያስፓራዎች ተሳታፊ እስኪሆኑ ድረስ እንዳይደረግ የሚጠይቅ ነው።
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።