በሺሆች የሚቆጠሩ የአፋር ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በሺሆች የሚቆጠሩ የአፋር ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ተገለፀ

የህወሓት ታጣቂዎች አሁንም ድረስ ተቆጣጥረዋቸዋል ከተባሉ የአፋር ክልል አካባቢዎች ባለመልቀቃቸው በሺሆች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ተፈናቃዮቹ ከፍተኛ የምግብና የህክምና እጥረት እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል።

“ድርማ” በተሰኘ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ አስተያት ሰጭዎች በበኩላቸው ታጣቂዎቹ አሉባቸው በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ስለሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ምንም ዓይነት መረጃ እንደማይደርሳቸው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።