የካሜሩኑ ፖል ቢያ 90 ዓመታቸውን አከበሩ

  • ቪኦኤ ዜና

ፖል ቢያ

በዓለም ባለ ትልቅ ዕድሜ የሃገር መሪ የሆኑትን የፕሬዝደንት ፖል ቢያ 90ኛ የልደት በዓልን ካሜሩን በማክበር ላይ ነች።

ደጋፊዎቻቸው ፖል ቢያ ከሁለት ዓመት በኋላ በሚደረገው ምርጫ ተሳትፈው አራት አስርት ዓመታትን ያስቆጠርው አገዛዛቸውን ይቀጥላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።

ተቃዋሚዎቻቸው በበኩላቸው ቢያ ፈላጭ ቆራች ናቸው በማለትና የጤንነታቸውን ሁኔታም በማንሳት በሥልጣን መቀጠላቸውን አይደግፉም።

የቪኦኤው ሞኪ ኤድውን ከያዉንዴ እንደዘገበው፣ ወጣቶች በቢያ የልደት በዓል አከባበር ላይ እንዲሳተፉ በመገደድ ላይ ናቸው።

ፖል ቢያ ካሜሩንን ከእ.አ.አ 1982 ጀምሮ ላለፉት 41 ዓመታት በፕሬዝደንትነት ሲመሩ ቆይተዋል።

ከእአአ 1992 ጀምሮ የተደረጉትን ምርጫዎች ሁሉ ቢያ ቢያሸንፉም፣ ተቃዋሚዎቻቸው ምርጫዎቹ የተጭበረበሩ ናቸው ሲሉ ይከሳሉ።

ቢያ በእአአ 2008 የሥልጣን ግዜን የሚገድበውን አንቀጽ ከሕገ-መንግስቱ ሰርዘው በሥልጣን እስከ አሁን መቆየት ችለዋል።

ዛሬ በተከበረው የልደት በዓላቸው ላይ ገዥው የካሜሩን ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ቢያ በመጪው ምርጫ እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

ቢያ በያኡንዴ በተደረገው የልደት በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ አልተገኙም። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የዕድሜና የጤና ሁኔታቸውን እያነሱ ዘግበዋል።