የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ጥያቄ እና የተሰጡት መልሶች

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ጥያቄ እና የተጡት መልሶች

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በተደረገ ውይይት አብዛኛው የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄዎች መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች።

የቤተክርስቲያኒቱን ፓትሪያርክ ጨምሮ ሊቃነጳጳሳትን ያካተተ ልዑክ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ዛሬ ባደረገው ውይይት ነው ለአብዛኛው ጥያቄዎች መልስ መሰጠቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሃፊ አቡነ ጴጥሮስ የገለጹት፡፡

በሌላ በኩል የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ሕገወጥ ነው የሚለው እና “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል የተቋቋመው አካል ለየካቲት 5 የጠራውን ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ማራዘሙን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቼ ለይቻቸዋለሁ ያለቻቸው አቡነ ሳዊሮስ በሰጡት መግለጫ፣ የእርቀ ሰላም ሂደቱን እንደሚደግፉም ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዕግድ ጥያቄ የቀረበለት ፍርድ ቤት፣ ቤተ ክርስቲያኗ በአወገዘቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱ ተገልጿል።

ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ በጥቂቱ 8 ሰዎች መገደላቸውን እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

ኢሰመኮ ሁሉንም ወገኖች እና የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለችግሩ እልባት ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።