ባህላዊ ውዝዋዜን ለአካል እና አዕምሮ ግንባታ ያዋለው "ኢትዮ-ዳንስ ፊትነስ"

Your browser doesn’t support HTML5

ቶማስ ሀይሉ የኢትዮጵያ ባህላዊ ውዝዋዜዎችን ከዘመናዊ ስፖርት መርሆች ጋር አዛምዶ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ወጣት ነው። ይህ ለየት ያለ አቀራራቡ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ በሚገኙ የስፖርት ማዕከላት ከ400 በላይ ሰዎችን ያሰለጥናል። በተለያዩ የኢትዮጵያ እና የባህርማዶ ከተሞች እየዞረ ሰዎች እየተዝናኑ ጤናቸውን እንዲጠብቁ የሚያግዝ "የስፖርት ኮንሰርት" የማሰናዳት ህልም ሰንቋል። ሀብታሙ ስዩም ቶማስን አነጋግሮታል። ።