እየተነቃቃ ያለው የኒው ዮርክ ቻይናታውን

  • ቆንጂት ታየ

Your browser doesn’t support HTML5

እየተነቃቃ ያለው የኒው ዮርክ ቻይናታውን

ኒው ዮርክ ማንሃተን የሚገኘው ትውልደ ቻይና እንደሚበዙበት የሚነገረው መንደር "ቻይናታውን" ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካሉት ዕድሜ ጠገብ የእስያ አሜሪካዊያን ቀበሌዎች አንዱ ነው።

አሁን አሁን ሠፈሩ እየተነቃቃ መሆኑ ይታያል።

በማኅበራዊ መገናኛው ላይ የተራቀቀው አዲሱ የእስያ አሜሪካዊ ትውልድ የቤተሰቡን የንግድ ድርጅቶችም በማስተዋወቅና ጎብኚዎችን ወደዚህ ልዩ አካባቢ በመሳብ ጥረት ተጠምዷል።

ይህ ቻይናታውን ሰፈር ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያስከተለው ጣጣ እንዲሁም የእስያዊ ጠል አመለካከት ሰለባ ሆኖ ቆይቷል።

ሪፖርተራችን ቲና ትሪን ከዚያው ያጠናቀረችውን ቆንጅት ታየ ለዛሬ አሜሪካና ህዝቧ ፕሮግራም ወደ አማርኛ መልሳዋለች።