የጳጳሳቱ ‘ሹመት’ እና ቅዱስ ሲኖዶስ

Your browser doesn’t support HTML5

የጳጳሳቱ ‘ሹመት’ እና ቅዱስ ሲኖዶስ

ሰሞኑን ተሰጠ በተባለው የ”ጳጳሳት ሹመት" ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ውሣኔ ያሳልፋል የተባለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ዛሬ እንደሚጀመር ተገልጿል።

በሌላ በኩል በቤተክህነት በርና በአካባቢው ጥበቃ ላይ ነበሩ ያሏቸው የፖሊስ አባላት መነሳታቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልፀው መንግሥት ፀጥታ እንዲያስከብር ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ “እስካሁን የፖሊስ ኃይል በየትኛውም የኃይማኖት ተቋም ላይ ተመድቦ የሚጠብቅበት አሠራር የለም” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ሥጋት መኖሩን የሚጠቁም መረጃ ከደረሳቸው ግን ወንጀልን ከመከላከል ተግባራቸው ጋር አቀናጅተው እንደሚይዙት ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ፡፡