ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ የካሜሩን ተገንጣዮችን ረድታችኋል በሚል ውንጀላ ለአንድ አመት ያህል ታስረው የነበሩ አምስት ሰራተኞቹን መለቀቅ በደስታ መቀበሉን ይፋ አስታውቋል።
የካሜሩን ጦር የአማጺው ተገንጣይ ቡድን አባል ነው ያለውን አንድ በጥይት ተመቶ የቆሰለ ሰው በማጓጓዛቸው ነበር የረድኤት ሠራተኞቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው።
ይሁን እንጂ ኤምኤስኤፍ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ማንኛውንም ሰው እንደሚረዳ ተናግሮ በተገንጣዮች በተያዙት አካባቢዎች ግን ከመንግሥት የጸጥታ ዋስትና ሲያገኝ ብቻ ሥራውን እንደሚቀጥል አመልክቷል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/