በትግራይ የጤና ተቋማት ሥራ እየጀመሩ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ የጤና ተቋማት ሥራ እየጀመሩ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ተናገሩ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መሃከል የሠላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በትግራይ ክልል አገልግሎት አቋርጠው ከነበሩት የጤና ተቋማት ውሰጥ 36ቱ የጤና ተቋማት ወደ ሥራ መግባታቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ምክንያት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ የመገንባት ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ “በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሌሎች ክልሎች ውስጥ የተጎዱትን የጤና ተቋማት መልሶ የመገንባት ሥራ ቀጥሏል” ብለዋል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/