በዋግ ኽምራና በአፋር ክልል ስር ባሉ የተወሰኑ ቀበሌዎች እርዳታ ማድረስ እንዳልተቻለ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዋግ ኽምራና በአፋር ክልል ስር ባሉ የተወሰኑ ቀበሌዎች እርዳታ ማድረስ እንዳልተቻለ ተገለፀ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ የሚገኙ ሁለት ወረዳዎችና በአፋር ክልል አስተዳደር ስር ያሉ ሦስት ቀበሌዎች እስካሁን በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በመሆናቸው ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስም ሆነ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አለመቻሉ ተገለጸ፡፡

ከሐምሌ 6/2013 ዓ.ም ጀምሮ መፈናቀላቸውን የገለፁት የአበርገሌና ጻግብዥ ወረዳ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉበት ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በሁለቱ ወረዳዎች ሰብአዊ ርዳታውን ለማድረስ ከዓለም አቀፍ ረጅ ተቋማት ጋር ውይይት መደረጉን ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በአፋር ክልል ኪልበቲረሱ ዞን መጋሌ ወረዳም በተመሳሳይ ሁኔታ የህወሓት ኃይሎች ሦስት ቀበሌዎች ውስጥ መኖራቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጭዎች ይህም ለሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትም ሆነ ለጸጥታ ችግር እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡