በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ኮሌራ አሁንም እንደቀጠለ ነው - ተመድ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ተከስቶ የነበረዉ የኮሌራ በሽታ ወደ አጎራባች ዞኖች እየተስፋፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ( ኦቻ) ገለፀ። በባሌ ዞን አምስት ወረዳዎችና በአጎራባች የሶማሌ ክልል የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ ጉጂ ዞን፣ ግርጃ ወረዳ መስፋፋቱንም ድርጅቱ ትላንት ባወጣዉ መግለጫ አመልክቷል ።