በሽረ የስልክ አገልግሎት በአጭር ቀን ውስጥ እንደሚጀምር ተገለፀ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በሽረ የስልክ አገልግሎት በአጭር ቀን ውስጥ እንደሚጀምር ተገለፀ

በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ የስልክ አገልግሎት እስከ ነገ ድረስ ሊጀመር እንደሚችል ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። አገልግሎቱን ለማስጀመር የፋይበር ኦፕቲክስ ዝርጋታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንንም የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከሽረ ቀጥሎ በአክሱምና በአዓድዋ ከተማ አገልግሎቱን ለማስጀመር ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ሽረን ጨምሮ በአካባቢው ላሉት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የጥገና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/