የነዳጅ ድጎማውና በተጠቃሚዎች የሚነሳው ቅሬታ

Your browser doesn’t support HTML5

የነዳጅ ድጎማውና በተጠቃሚዎች የሚነሳው ቅሬታ

የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈው ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሸከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ቢያደርግም ተገልጋዩ ለተጨማሪ ወጭ መዳረጉን አስተያየት ሰጭዎች ገለጹ፡፡

አስተያየታቸውን ለቪኦኤ የገለፁ በደሴና በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ “በርካታ የተሸከርካሪ ባለሃብቶች ከመንግሥት የሚደረገውን የነዳጅ ድጎማ ተቀብለው የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጡም፡፡ ቢሰጡም የሚጠይቁት የተጋነነ ዋጋ ነው” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በቀለች ጉማ፤ የነዳጅ ድጎማ ተጠቅመው አገልግሎት የማይሰጡ ካሉ ጥናት ተደርጎ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/