ተጨማሪ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ተጨማሪ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ነው

የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ያደረጉትን የሠላም ሥምምነት ተከትሎ ተጨማሪ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ መሆኑን ለጋሽ ድርጅቶች እየገለጹ ነው።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩኤንኤችሲአር)፣ የተለያዩ የሕይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ዛሬ ትግራይ ክልል መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ደግሞ ቅዳሜ ዕለት መቀሌ እና ሽሬ ከተሞች የእርዳታ ምግብና ነዳጅ ማድረሱን ገልጾ፣ ተደራሽነቱን በየቀኑ ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በአየር በረራም ዕርዳታ እያደረሱ መሆኑን ለጋሽ ድርጅቶቹ ገልጸዋል፡፡

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/