የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ዩክሬንን ለመጎብኘት ዛሬ በድንገት ኪቭ ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ወዲህ የመጀመሪያቸው በሆነው በዚህ ጉብኝታቸው ኪቭ ሲደርሱ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ በረዶ እየጣለ ከነበረበት የቤተመንግሥታቸው ደጃፍ ወጣ ብለው የተቀበሏቸው መሆኑን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ሁለቱም የቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቦሪስ ጆንሰንና ሊዝ ትረስ ከዘለንስኪ ጋር የተገናኙ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ሱናክም በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት "ብሪታኒያ እስከ መጨረሻው ከዩክሬን ጋር ናት" ብለዋል፡፡
ብሪታኒያ እስካሁን ለዩክሬን የ2.7 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ መስጠቷ ተዘግቧል፡፡