የቱኒዚያውን ፕሬዘዳንት ሳዒድን የሚቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላት ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ

በቱኒሲያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ፕሬዘዳንት ሳዒድን በመቃወም የወጡ ሰልፈኞች

በቱኒሲያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ፕሬዘዳንት ሳዒድን በመቃወም የወጡ ሰልፈኞች

በቱኒዝያ የምግብ እና የነዳጅ እጥረት የተነሳ እየጨምረ በመጣው የህዝብ ቁጣ መሃል የሃገሪቱ ፕሬዘዳንት ካይስ ሰዒድ የፖለቲካ ስልጣናቸውን ለማጠናከር ያደርጉትን እንቅስቃሴ በመቃወም ሁለት ተቀናቃኝ ድርጅቶች እስካሁን ድረስ ከተደርጉ ሁሉ የገዘፈ ተቃውሞ አካሄዱ።

የእስላማዊው የአኢናሃዳ ፓርቲ እና የነጻ ሕገመንግስታዊ ፓርቲ ደጋፊዎች በዋና ከተማዋ ቱኒዝ አጎራባች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉባቸው የሳዒድ አስተዳደር የምጣኔ ሃብት አያያዝ ጉድለት እንዳለው እና “ጸረ ዴሞክራሲ” የሆነ መፈንቅለ መንግስት አድርጓል የሚሉ ትላልቅ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሂደዋል።

የቱኒዚያ ፓርላማ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ ከተዘጋ በኋላ በህዝበ ውሳኔ በጸደቀው አዲስ ህገ መንግስት በአዋጅ ወደ ስልጣን የመጡት ሰዒድ ስልጣናቸውን እያስፋፉ ሲሆን የቱኒዚያን የዓመታት ቀውስ ለመታደግ እርምጃው አስፈላጊ ነበር ብለዋል።

በቲኒዝ በዚህ ሳምንት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ወረዳዎች በፖሊስ እና በተቃውሞ ሰልፈኞች መሃከል የተወሰኑ ግጭቶች የተስተዋሉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በዋና ከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖሊስ አባላት ተሰማርተው ውለዋል።