ስለ ዘንድሮው የብሄራዊ ፈተና ፈተናዎች የተሰጡ አስተያየቶች

Your browser doesn’t support HTML5

ስለ ዘንድሮው የብሄራዊ ፈተና ፈተናዎች የተሰጡ አስተያየቶች

ቀጣይ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኞች ራሳቸውን ከአሉባልታ በማቀብ በፈተናቸው ላይ ብቻ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በባህር ዳር ከተማ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች፣ በርካታ ተማሪዎች ፈተናውን ያቋረጡት በዋናነት ባልተረጋገጡ የአሉባልታ መረጃዎች ነው ብለዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከተፈተኑ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መካከል ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት ፈተናውን ማቋረጣቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከጥቅምት 8 ጀምሮ ለፈተና ይቀመጣሉ፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]