ቆቦ ከሳምንታት ጦርነት በኋላ ወደ መረጋጋት እየተመለሰች ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ቆቦ ከሳምንታት ጦርነት በኋላ ወደ መረጋጋት እየተመለሰች ነው

ቆቦን ጨምሮ ጦርነት ሲካሄድባቸው የነበሩ በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ አካባቢዎች ቀስ በቀስ ወደ መረጋጋት እየተመለሱ መሆናቸውንና አንጻራዊ ሠላም መስፈኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

አካባቢው በተደጋጋሚ የጦርነት ቀጠና በመሆኑ የብዙዎች ህይወት አልፏል፣ በመቶ ሽዎች ተፈናቅለዋል፣ በሚሊዮን የሚገመት ሃብትና ንብረት ወድሟል የሚሉት ነዋሪዎች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግለትም ጠይቀዋል፡፡

ህወሓት በበኩሉ ታጣቂዎቹ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በንብረት ውድመት ስለመሳተፋቸው የሚገልጹ ውንጀላዎችን በተደጋጋሚ አስተባብሏል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]