በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች መዝገብ የሰፈረው የገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል ነገ በአዲስ አበባ በድምቀት እንደሚከበርም ተገልጿል።
ዛሬ በዋዜማው ከነበሩ ድምቀቶች አንዱ የሆነው አስር ሺ የቡና መጠጫ ሲኒዎችን የያዘው ረከቦት የተመልካቾችን ትኩረት ስቧል።
በዓሉን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እሬቻ የሠላም የአንድነት እና የወንድማማችነት ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]