ሰሜን ወሎ ላይ በርካታ ሺህ አዲስ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ይሻሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ሰሜን ወሎ ላይ በርካታ ሺህ አዲስ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ይሻሉ

በትግራይ ክልል ሽሬ እና መቀሌ ከተሞች ለሚገኙ 23,000 አዲስ ተፈናቃዮች የመጠለያ አቅርቦቶች ማንቀሳቀሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ አስታውቋል።

ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው መርሳ ከተማ ለሚገኙ ወደ 12 ሺ የሚጠጉ ተፈናቃዮች ደግሞ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን ማሠራጨት እንደሚጀምር ጠቁሟል።

በተለይ ከቆቦ ከተማና አካባቢው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን የገለጸው የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር በበኩሉ በዩኤን ኦቻ የተጠቀሱትን ጨምሮ እስከዛሬ ድረስ 92ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]