"በኤርትራ ሠራዊት ዓዲግራት ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ተፈጽሟል" የአካባቢው የሆስፒታል ምንጮች

Your browser doesn’t support HTML5

"በኤርትራ ሠራዊት ዓዲግራት ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ተፈጽሟል" የአካባቢው የሆስፒታል ምንጮች

“የኤርትራ ሠራዊት ዓዲግራት ከተማን ጳጉሜ 2/2014 በከባድ መሣሪያ ደብድቦ ሦስት ህፃናት የሚገኙባቸው አምስት ሰዎች ሲገደሉ 14 ደግሞ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲሉ የዓዲግራት ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ መናገራቸውን ሪፖርተራችን ዘግቧል።

ሪፖርተራችን አዲግራት ሄዶ በድብደባው ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለፁና ሆስፒታል የተኙ ሰዎችንና የሆስፒታሉን ሠራተኞችንም አነጋግሯል።