የአሁኑ ጦርነት ያስከተለው የህፃናት ሞትና መፈናቀል

በሰሜን ኢትዮጵያ ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ የተፈናቀሉ የተጠለሉበት በአፋር ክልል ሰመራ 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ጉያህ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እአአ በ5/17/2022

በሰሜን ኢትዮጵያ ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

ህወሓት በያሎ ከተማ ላይ ተኩሷል ባሉት ከባድ መሣሪያ ሦስት ሕፃናት መገደላቸውንና የቆሰሉት በዱብቲ ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸውን የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና የምግብ ዋስትና ኮሚሽነር መሀመድ ሁሴን ለአሜሪካ ድምፅ አክለው ገልፀዋል።

በአካባቢው በተፈፀመው ድብደባ ሕፃናትን መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ አመልክቶ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጥሪ አሰምቷል።

ህወሓት ሲቪሎችን ዒላማ በማድረግ የሚቀርቡበትን ውንጀላዎች በተደጋጋሚ ያስተባብላል።

በሌላም በኩል ካለፈው ሣምንት ጀምሮ በአስቸጋሪ ሰብዓዊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ሰሞኑን ከቆቦ ከተማ የተፈናቀሉ ተናግረዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Your browser doesn’t support HTML5

የአሁኑ ጦርነት ያስከተለው የህፃናት ሞትና መፈናቀል