አዲስ ፓወር ሃውስ በሴት በጎ ፈቃደኛ የስርዓተ ጾታ ባለሞያዎች አማካኝነት ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረ የድረ-ገጽ የመወያያ መድረክ ነው። ፌስ ቡክ እና የዩቱብ ገጾች አማካኝነት በተለያዩ የስርዓተ ጾታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነጻ የዲጂታል መጽሄቶችን ያዘጋጃል። በዩቱብ ላይ ያሉ ሃሳቦችም መስማት የተሳናቸውን ባማከለ መልኩ በምልክት ቋንቋ ተተርጉመው እንዲቀርቡ ያደርጋል።
የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑ ሴቶች በጾታዊ ጥቃት፣ በፍቅር እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን የሚጋሩበት የተለያዩ ነጻ የዲጂታል ህትመት ውጤቶችን አዘጋጅቷል። ቡድኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍቃድ በማውጣት ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ ሲሆን በስርዓተ ጾታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን በመስራት፣ ወጣቶች የሚወያዩበት መድረክ በመክፈት እና በከፍተኛ ግብረሰናይ ተቋማት እና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶች መሃከል እንደ ድልድይ በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ የቡድኑ መስራች ሃና ለማ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግራለች።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/