በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ በመቶ መጨመሩን የገለጸው ቢሮው ባለፈው ዓመት በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 157 ሺህ ገዳማ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ከ251 ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸውን የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ጉዲሳ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
በክልሉ አራት ከተሞች፣ አስራ ሦስት ዞኖች እና 65 ወረዳዎች ውስጥ የበሽታው ሥርጭት እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም በከተማቸው በሽታው መስፋፋቱን ይገልፃሉ።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/