ለአማራ ክልል የቀጠለው የአሜሪካ ድጋፍ

Your browser doesn’t support HTML5

ለአማራ ክልል የቀጠለው የአሜሪካ ድጋፍ

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአማራ ክልል ከ430 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማፍሰሱንና ድጋፉ እንደቀጠለ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናግረዋል።

የዚሁ ድጋፍ አካል በሆነ እርምጃ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ሥራአመራር ወጣት ባለሞያዎችን ለማሰልጠን የሚውል ወደ ስምንት ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ዛሬ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ውስጥ ይፋ አድርገዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ባሕር ዳር ውስጥ የተጠለሉትን የጎበኙትና ተጨማሪ እርዳታ እንደሚደረግ የገለፁት የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር “ዋናው ነገር ግን ሁላችንም ለሠላም መፀለያችንን መቀጠል አለብን” ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።