ማሊ በአይቮሪ ኮስት ወታደሮች ላይ ክሥ መሠረተች

  • ቪኦኤ ዜና

ማሊ ውስጥ በቅጥር ተዋጊነት ተወንጅለው የታሰሩ አርባ ዘጠኝ የአይቮሪ ኮስት ወታደሮች የአገር ፀጥታ በማደፍረስ ወንጀል ክሥ ተመሠረተባቸው።

ይህንኑ ከትናንት በስተያ፤ ዕሁድ ያስታወቁት የማሊ ፀረ-ሽብር ልዩ ግብረ ኃይል አቃቤ ህግ ናቸው።

አይቮሪ ኮስት ባለፈው ሐምሌ መጀመሪያ ማሊ ዋና ከተማ ባማኮ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ ታስረው የሚገኙት ወታደሮቿ እንዲለቀቁ ስትጠይቅ ቆይታለች።