ኦሮምያ ውስጥ ያልተሻሻሉ የመብቶች አያያዞች

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮምያ ውስጥ ያልተሻሻሉ የመብቶች አያያዞች

የኦሮምያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈፀሙ እሥራቶችና የተያዙ ሰዎችን መብቶች የሚጥሱ አሠራሮችን መመልከቱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የተሻሻሉ አያያዞችና አሠራሮች መኖራቸውንም ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ከጠቀሳቸው አሉታዊ ሁኔታዎች መካከል የሰዎች ከህግ አግባብ ውጭ መታሰር፣ ሕጉ በሚፈቅደው ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት አለመቅረብና የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አለመፈፀም ይገኙባቸዋል።

ኮሚሽኑ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤቶች ላይ ያዘጋጀውን የክትትል ግኝቶች ሪፖርት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ።