በኢትዮጵያ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ያለክልከላ ርዳታ ማዳረስ እንዲቻል፣ የሰላም ውይይት ለማካሄድ የሚደረገው ጥረት መሻሻል እንዲታይበት ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር ግፊት እያደርጉ ነው።
ያሳለፍነው አርብ ወደ አዲስ አበባ ያመሩት ሃመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋራ መነጋገራቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በትዊተር ገፁ አስታውቋል።
ያልተቆራረጠ ሰብዓዊ ርዳታ የማድረስ፣ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እንዲሁም ግጭቱን ለማስቆም እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ፖለቲካዊ ውይይት የማካሄድ አስፈላጊነት ላይ መነጋገራቸውን ገልጿል።
ማይክ ሃመር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የፖለቲካ እና በሰብዓዊ መብቶች ላይ ከሚሠሩ ድርጅት መሪዎች ጋራ መወያየታቸው ታውቋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/