በጦርነት እና አለመረጋጋት የተፈተነው የኢትዮ ቴሌኮም ትርፋማነት

Your browser doesn’t support HTML5

በጦርነት እና አለመረጋጋት የተፈተነው የኢትዮ ቴሌኮም ትርፋማነት

ኢትዮ ቴሌኮም፣ በሀገሪቱ በነበረው ጦርነት እና አለመረጋጋት ምክንያት የገቢ ዕቅዱን ማሳካት እንዳልቻለ አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም፣ በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች በነበሩት አለመረጋጋቶች እና በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠመው ጦርነት ምክንያት፣ ከ3ሺሕ4 መቶ በላይ የሞባይል ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውን ገልጿል፡፡

በዚኽም ሳቢያ፣ በዘንድሮው የበጀት ዓመት የገቢ ዕቅዱን እንዳያሳካ ክፍተት እንደፈጠረበት አስረድቷል፡፡ በበጀት ዓመቱ በጦርነት እና አለመረጋጋት የተፈተነው ተቋሙ እንደዚያም ኾኖ፣ 61 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/