ወደ ዳባት ካምፕ የተወሰዱ ኤርትራውያን ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

ወደ ዳባት ካምፕ የተወሰዱ ኤርትራውያን ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ

የዛሬ አስር ቀን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ተሳልመው ሲመለሱ ለገጣፎ አካባቢ በፖሊስ የተያዙትና በግድ ታፍሰው ወደ ዳባት ካምፕ የተወሰዱት ኤርትራውያን “እስካሁን ድረስ ቀለብ ስላልተሰጠን፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን” ሲሉ አስታውቀዋል።

ታፍሰው ከተወሰዱት ሰዎች መካከል የሚያጠቡ እናቶች፣ በመድሐኒት የሚኖሩ ህመምተኞች እና የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ሰዎች እንደሚገኙበት ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ሰዎች ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት እንዲሁም ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘ ምላሽና አስተያየት ባይኖርም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግን ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/