በሁለቱ ወለጋ ዞኖች ከጭፍጨፋ የተረፉት እርዳታ እየጠየቁ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በሁለቱ ወለጋ ዞኖች ከጭፍጨፋ የተረፉት እርዳታ እየጠየቁ ነው

በኦሮምያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በቅርቡ በታጣቂዎች ከተፈፀመ የብሄር ማንነት የለየ ጅምላ ግድያ የተረፉና መቻራ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናገሩ።

ወደ የመንደራቸው እንዲመለሱ የአካባቢው ባለሥልጣናት ቢጠይቋቸውም ተፈናቃዮቹ ግን የበረታ ሥጋት እንዳለባቸውና መመለስ እንደማይፈልጉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ጭፍጨፋውን ተከትሎ ከለምለም ቀበሌ ውስጥ በሥጋት ተፈናቅለው ከነበሩ ቁጥራቸው ወደ ሃያ አምስት ሺህ ከሚጠጋ ሰዎች ብዙዎቹ መመለሳቸውን ቀደም ሲል የክልሉ አደጋ መከላከል የነበረውና አሁን ስሙን ወደ ቡሳ ጎኖፋ ግን ገልጿል።