በሶማሊያ በከባድ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ቢያንስ አምስት መቶ ህፃናት ሞቱ

Your browser doesn’t support HTML5

በበርካታ ዓመታት ባልታየ ደረጃ ከባድ በሆነው ድርቅ በተጠቃችው በሶማሊያ በዚህ የአውሮፓ 2022 በተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ሳቢያ ቢያንስ አምስት መቶ ህጻናት መሞታቸውን ዩኒሴፍ ተናገረ። በሪፖርቶች ውስጥ ያልተካተቱ እና በየቤቱ እንዲሁም እርዳታ ለመፈለግ በመወሰድ ላይ ሳሉ መንገድ ላይ ሕይወታቸው ያለፈ በርካታ ህፃናት እንዳሉ አክሎ ገልጿል። በመሆኑም የሞቱት ህጻናት ቁጥር በይፋ ከተመዘገበው በእጅጉ ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/