አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት መማረራቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት መማረራቸውን ገለፁ

በነዳጅ እጥረት ምክኒያት መማረራቸውን የገለፁ አሽከርካሪዎች፤ “በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያላቸው በመደበቅ ወይም ሳይጨርሱ ጨርሰናል በማለት በመላ ሃገሪቱ እጥረት እንዲከሰት አድርገዋል” ሲሉ ወቅሰዋል። መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በነዳጅ እጥረቱ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም የከተማ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ መስተጓል ተፈጥሯል ብለዋል።

የአስተዳድሩ ንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አሚኑ ጣሃ፤ “ሰሞኑን በአገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች እና በታክሲዎች ሰልፍ መንገዶቿ የሞሉባት የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈላጊውን ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንና የሰልፉ መብዛት መንስዔም በሌሎች ኣካባቢዎች እንደ ድሬዳዋ ቁጥጥር እየተደረገና ነዳጅ እየቀረበ ስላልሆነ ነው” ብለዋል።