አፍሪካ ነክ ርዕሶች

Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪካ ነክ ርዕሶች

በዛሬው ሳምንታዊው የ”አፍሪካ ነክ ርዕሶች” ፕሮግራም ሦስት ጉዳዮችን እናነሳለን።

· ግጭት፣ የአካባቢ አየር መለወጥ፣ የኮቪድ 19 ወረሽኝ እና እጅግ እያሻቀበ የመጣው የምግብ፣ የነዳጅና የማዳበሪያ ዋጋ ሳህል በመባል በሚታወቀው የአፍሪካ ክልል በስላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያሳስባል።

· በሚቀጥለው ወር ፕሬዚዳንቷን በምትመርጠው ኬንያ ከዚህ በፊት በምርጫ ወቅቶች የተከሰቱና የሰው ህይወት የቀጠፉ ብጥብጦች መልሰው እንዳይከሰቱ ስጋት አለ። ህይወታቸው የተቀጥፉትንና ከሁከቱ የተረፉትን ቤተሰቦች የሚወክለው የእናቶች ቡድን ሁሉም ወገኖች ለሰላም ተገዢ እንድሆኑ ጥሪ በማድረግ ላይ ነው።

· የሃይል ማመንጫ ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን ለሰዓታት የኤሌክትሪክ ሀይል እንደማያገኙ በደቡብ አፍሪካ በመንግሥት የሚተዳደረው የኤሌክትሪክ ሃይል ባለሥልጣን አስታውቋል።

ዝግጅቱን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።