በመቶዎች የሚቆጠሩ የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተናንቀዋል

  • ቪኦኤ ዜና

ፋይል -የሱዳን ተቃዋሚዎች በዋና ከተማዋ ካርቱም የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ

በሱዳን ስልጣን ላይ ያለው ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ እና የሲቪል መንግስት እንዲመሰረት የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በዋና ከተማዋ ካርቱም ዋና መንገዶች እና ከከተማዋ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ለአራተኛ ቀን ሰልፍ አካሂደዋል።

ሀሙስ እለት ከፍተኛ ህዝብ የተሳተፈበትን ሰልፍ የፀጥታ ኃይሎች በጉልበት ለመበተን ሞክረው ዘጠኝ ሰው የተገደለ ሲሆን በጥቅምት ወር በአብደል ፈታህ አልቡራን የሚመራው ወታደራዊ ሀይል ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ ወራት ከተካሄዱ ሰልፎች በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ቀን ሆኗል።

በቅርቡ በተካሄዱ ሰልፎች ተቃዋሚዎች ጎማዎችን ያቃጠሉ እና ሸክላ ጡቦችን በመደርደር መንገድ የዘጉ ሲሆን የፀጥታ ሀይሎች ደግሞ ጥይት፣ አስለቃሽ ጋዝ እና ሀይል ያለው የውሃ መድፍ መጠቀማቸውን የተባበሩት መንግስታት እና የህክምና ባለሙያዎች አስታውቀዋል።