በአፋር ካምፖች ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ካምፖች ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ጠየቀ

በአፋር ክልል ሰመራና አጋቲና ካምፖች ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል።

“ሰዎቹን እንደ እሥረኛ ሳይሆን እንደ ተፈናቃዮች ነው የምናያቸው” ያለው የአፋር ክልል መንግሥት በበኩሉ “ከነበሩበት ሰብስበን ያመጣናቸውም ለደህንነታቸው ስንል ነው፤ አሁንም አደጋ እንዳይደርስባቸው እየጠበቅናቸው ነው” ብሏል።

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሰዎቹን መያዝ አስመልክቶ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ህገወጥና በብሄር ማንነታቸው ላይ የተመሠረተ ነው፤ የዘፈቀደ እሥር በመሆኑም በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል” ብለዋል።

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።