በወለጋው ጥቃት የተገደሉት 338 ሰዎች መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በወለጋው ጥቃት የተገደሉት 338 ሰዎች መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ

ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ እስከ ትናንት ድረስ ከኦሮምያ ክልል የደረሳቸው መረጃ 338 ሰው መገደሉን እንደሚያሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ተናግረዋል።

በጥቃቱ ስለተገደሉት ኀዘናቸውን የገለፁት የፕሬስ ኃላፊዋ ሠላምና ፀጥታ የመንግሥት ቁልፍና ቀዳሚ አጀንዳ መሆናቸውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል “በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ግጭት ለመፍታት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራ የሠላም ሂደት ኢትዮጵያ እጅግ ቁርጠኛ ናት” ብለዋል የፕሬስ ኃላፊዋ።

ህወሓት በበኩሉ በኬንያ መንግሥት ሰብሳቢነትና አስተናጋጅነት በሚካሄድ ድርድር ላይ ለመቀመጥ ዝግጁ መሆኑን ቀደም ሲል አስታውቆ ነበር። ስለዚሁ የተጠየቁት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ የኬንያው ፕሬዚዳንትም በአፍሪካ ሕብረት የሚመራውን የሠላም ጥረት እንደሚደግፉ ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ፋይል ያዳምጡ።