- ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ በቁጥጥ ስር ውሏል
የፍትህ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ሰኔ 21/2014 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በዐቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ የክስ መዝገቡ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መከፈቱን ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ አረጋግጠዋል
ጋዜጠኛ ተመስገን የክስ መዝገቡ ወደ ተከፈተበት ፍርድ ቤት የተወሰደ ቢሆንም፣ ዳኛ ባለመኖሩ ምክንያት ችሎት አለመቅረቡን ጠቅሰው፣ ክሱ በነገው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ገልጸዋል፡፡
በሌላ ዜና የ“ኢትዮፎረም” አዘጋጅ የነበረው ያየሰው ሽመልስ ደግሞ በዋስ ከተፈታ ከሳምንት በኋላ ዛሬ በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውሏል። ያየሰው የፀጥታ ኃይል አባል መሆናቸውን በተናገሩ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከቤቱ ዛሬ ጠዋት መያዙን የገለጹት ጠበቃው አቶ ታደለ ገብረ መድህን፣ እስካሁን ያለበት እንደማይታወቅ ተናግረዋል፡፡
/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Your browser doesn’t support HTML5