ባይደን የሴኔጋልን ፕሬዚዳንት አነጋገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች በጀርመን ቢቫሪያን አልፕስ ጉባዔ እአአ ከሰኔ 26 እስከ 28/2022 በሚካሄደው የቡድን ሰባት የበለፀጉ ሀገራት ጉባኤ ላይ ከሌሎች የሀገሮች መሪዎች ጋር።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ ተገናኝተው መነጋገራቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ።

ሁለቱ መሪዎች የሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑቲን ዩክሬን ላይ የሚያካሂዱት ጦርነት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ ስላሳደረው ጫና የተወያዩ ሲሆን ፕሬዚዳንት ባይደን ቡድን ሰባት በምግብ ዋስትና ረገድ ስለሚሰጠው ቀጣይ ድጋፍ መግለጫ የሚሰጥበት መሆኑን አንስተው ገለጻ እንዳደረጉላቸው የኋይት ሀውሱ መግለጫ አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ባይደን እና ፕሬዚዳንት ሳል የቡድን ሰባትን የዓለም አቀፍ መሰረተ ልማት እና ኢንቬስትመንት አጋርነት ሥራዎች በተመለከተም ተወያይተዋል።

ከዚህም መካከል አንዱ ሴኔጋል ውስጥ በሚከፈተው እና በየዓመቱ ብዙ ሚሊዮን የኮቪድ-19 እና የሌሎችም በሽታዎች በሚያመርተው አዲስ የክትባት ማምረቻ ኢንዱስትሪ መዋዕለ ነዋይ ለመመደብ የተያዘው ትልቅ ዕቅድ መሆኑን መግለጫው አውስቷል።