የአባቶች ቀን እንዴት መከበር ጀመረ?

ቅዳሜ ፣ ሰኔ 18.2022 የተነሳው ምስል "ለአባቶች ቀን" ማስጌጫ የሚቸረቸርበትን የሎስ ኤንጀልስ ጎዳና ገጽታ ያሳያል

አሜሪካዊያን በ’ያመቱ በወርሐ ሰኔ ሶስተኛ እሁድ የሚዘከረው የአባቶች ቀንን እያከበሩ ይገኛሉ። ይሄ ቀን የቤተሰብ አባላት ለአባቶች ያላቸውን ክብር የሚገልጹበት ፣ አባቶችን በስጦታ የሚያንቆጠቁጡበት ፣ ሬስቶራንቶች አባቶችን ለግብዣ ይዘው በወጡ ቤተሰቦች የሚጨናነቁበት ነው ።

ሂስቶሪ ዳት ካም History.com የተሰኘው ታሪክ መዝጋቢ አውታር የመጀመሪያው የአባቶች ቀን የተከበረው በጎረጎሳዊያኑ ሐምሌ 5/1908 እንደሆነ ይጠቁማል። በወቅቱ በምዕራብ ቨርጂኒያ የሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን በሞሞንጋ በሚባል ስፍራ ፌርሞንት የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ላይ በደረሰ ፍንደታ ህይወታቸውን ላጡ 362 ወንዶች መታሰቢያ ስነ-ስርዓት አዘጋጀ ። ስነስርዓቱ አንዴ እንዲደረግ እንጅ በ’ያመቱ እንዲከናወን የታቀደ አልነበረም ።

አውታሩ እንደሚያወሳው ፣ በቀጣዩ ዓመት ሶኖራ ስማርት ዶድ የተባሉ ከ5 የቤተሰብ አባላቶቻቸው ጋር ሚስታቸውን ባጡ አባት ያደጉ ሴት የስፖኬን-ዋሺንግተን ነዋሪ፣ በ’ያመቱ የአባቶች ቀን እንዲከበር ማህበረሰቡን ማግባባት ጀመሩ ። ተሳካላቸው ። በ1910 የዋሺንግተን ግዛት የመጀመሪያውን ግዛት አቀፍ የአባቶች ቀን አከበረ።

ይሄ ስነ-ስርዓት ቀስ በቀስ በመላ አሜሪካ ተስፋፋ ። አውታሩ በያመቱ አሜሪካዊያን በዚህ ቀን ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ለአባቶች ለሚሰጥ ስጦታ እንደሚያወጡ አስታውቋል ።