ከቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

ከቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ

ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ በነበረው ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተጠልለው ከነበሩ ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናገሩ።

በአማራ ክልል ጓንጓ ወረዳ በግለሰብ ቤቶች እና ቻግኒ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ከነበሩ ከ75ሺ በላይ ተፈናቃዮች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ባለፍት ሁለት ወራት ውስጥ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።

የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ መንግሥት በአካባቢው ሰላም ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ገልፀዋል።

ዘገባው የአስቴር ምስጋናው ነው።