ድርቁ የሶማልያን ከፊል ህዝብ ጎድቷል፣ ረሀብ በሶማልያ እያንዣበበ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ድርቁ የሶማልያን ከፊል ህዝብ ጎድቷል፣ ረሀብ በሶማልያ እያንዣበበ ነው

ትናንት ሰኞ በሞቃድሾ በተደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተመለከተው የሶማሊያ ሰብአዊ ጉዳዮች ልኡካን ቡድን ሶማልያ ውስጥ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እስከዛሬ ከፍተኛ በሆነው ድርቅ ተጠቅተዋል፡፡

አብዱርሃማን አብዲሸኩር ዋርሳሜ በድርቁ እየተጎዳ ያለው ህዝብ የሶማልያን ህዝብ ግማሽ ሊያክል ምንም አልቀረውም ይላሉ፡፡

ዋርሳሜ ድርቅ ከ84ቱ የሶማሌ አውራጃዎች 72 ያህሉን ጎድቷል ብለዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ስድስት የሚሆኑት በከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጠቁ በመሆናቸው ከወዲሁ ከፍተኛ ረሃብ በመሰለ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ዋርሳሜ "ሰዎቻችን አሁን መሞት ጀምረዋል፡፡ ሞት ጀምሯል፡፡

ረሀብ በአንዳንድ አካባቢዎች እያንዣበበ ድርቅም ወደ ረሀብ እየተቀየረ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ሶማልያውያን አንዳንድ ኃላፊነቶችን በመውሰድ ሊያግዙን ይገባል፡ " ይላሉ

ልኡካን ቡድኑ በረሃብ የሞቱት ሶማሌዎች ምን ያህል እንደሆኑ በቁጥር አልገለጹም፡፡ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ግን እገዛ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ ዋርሳሜ አሁን ያለው ድቅር "በአርባ ዓመት ውስጥ የከፋው ነው፡፡ ወደ 700ሺ የሚጠጉ ሶማልውያውያንን ከየገጠሩ እያፈናቀለ በየከተሞች አቅራቢያ እንዲሰፍሩ አድርጓል" ይላሉ፡፡

ዋርሳሜ እንደሚገልጹት የተባበሩት መንግሥታትና የረድኤት ድርጅቶች 1.4 ቢሊዮን ዶላር የጠየቁ ሲሆን ከእዚህ ውስት ያገኙት 58 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶቹ ብዙ ትኩረት የሰጡት ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ ለሩሲያው የዩክሬን ጦርነት፣ ለአፍጋኒስታን፣ ለሶሪያና የመን ቀውሶች መሆኑን ዋርሳሜ ተናግረዋል፡፡

የሰብአዊ ጉዳዮች ልኡካኑ ጨምረው እንደገለጹት ባላፈው ዓመት ሳደረግ ቀርቶ ዘንድሮ የተደረገው የሶማልያ ምርጫ ብዙ ትኩረት ያገኘ በመሆኑ ለሰብአዊ እርዳታው ምንም ትኩረት አልተሰጠውም፡፡

ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ትናንት ሰኞ በሰጡት ማስጠንቀቂያ "በሶማሊያና አጎራባች አገሮች ኢትዮጵያና ኬንያ ያለው የረሀብ ሁኔታ እየጠና ነው፡፡"

የሜትሮሎጂና የረድኤት ድርጅቶች እንደሚሉት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለአምስተኛ ጊዜ የዘለቀው የዝናብ ወቅት አንድም ጊዜ በቂ ዝናብ አልጣለም፡፡

የቪኦኤው መሀመድ ሼክ ኑር ከሶማልያ መዲና ሞቃድሾ ያደረሰንን ዘገባ ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡