ሀሪኬይን አጋታ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ከባድ የውቂያኖስ ማዕበል ደቡብ ምዕራባዊ ሜክሲኮ ላይ መጠነ ሰፊ ዝናብ ካወረደ በኋላ ዛሬ ማምሻውን ጋብ ይላል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ትናንት አጋታ በደቡቧ ዋሃካ ክፍለ ሀገር ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ ብዙ አካባቢዎችን በጎርፍ እና በጭቃ ናዳ አጥለቅልቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የሀሪኬን ክትትል ማዕከል እንዳለው እአአ በ1949 ክትትል እና ምዝገባ ከተጀመረ ወዲህ ግንቦት ወር ውስጥ በዚህ ደረጃ የከበደ የውቅያኖስ ማዕበል እና ዝናብ ተከስቶ አያውቅም።