ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህል እንዳልተሰበሰበ እና እንዳልተመረተ አማራ ክልል ገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህል እንዳልተሰበሰበ እና እንዳልተመረተ አማራ ክልል ገለፀ

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለፈው ዓመት የምርት ወቅት ቢባክንባቸውም ለዘንድሮው ግን እየተዘጋጁ እንደሆነ ጦርነት በተካሄደባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት ባለማምረታቸው እና ያመረቱትን ምርትም በጦርነቱ ምክንያት ባለመሰብሰባቸው የተፈጠረውን ክፍተት በቴክኖሎጂ ታግዘዉ ለመሙላት እንደሚሠሩም አርሶ አደሮቹ ገልፀዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ እንዳለው በጦርነቱ ምክንያት ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህል አልተመረተም፣ አልተሰበሰበም ወይም ተዘርፏል።

ጦርነቱ በምርት መጠን ላይ ያደረሰው ጉዳት ከባድ ቢሆንም ግብርናውን በማዘመን የተሻለ ነገር ለመሥራት መታቀዱን የክልሉ መንግሥት 136 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች ባስረከበበት ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናግረዋል።

ዘገባው የአስቴር ምስጋናው ነው።