ፊንላንድ እና ስዊደን የቱርክን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ቅድመ ሁኔታ ካላሟሉ ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ጥያቄመቃወማቸውን እንደሚቀጥሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬቺፕ ታይፕ ኤርዶአን ተናገሩ። የጉዳዩ ተንታኞች እንደሚሉት፣ኤርዶአን ለሚያሳስባቸው ጉዳይ ምን አልባት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ትኩረት ፈልገው ሊሆን ይችላልብለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ተከትሎ ፊንላንድ እና ስዊደን የኔቶ አባል ለመሆን ላቀረቡት ጥያቄ ቱርክተቃውሞዋን እንድታነሳ ለማድረግ ምን እንደምትፈልግ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ለማጣራት እየጣሩ ነው።
ሀሙስ እለት ከቱርክ አቻቸው ጋር በኒው ዮርክ ተገናኝተው የተነጋገሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒብሊንከን በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት እና የፊንላንድ እና ስዊድንን ማመልከቻ አንስተው ተወያይተዋል። ቱርክ ሁለቱሀገሮች የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳኑን (ኔቶን) እንዳይቀላቀሉ የተቃወመችው ቱርክ አሸባሪ ብላ የፈረጀቻቸውየኩርድ ተዋጊዎችን ያስጠልላሉ፣ በገንዘብም ይደግፋሉ በማለት ነው።
የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስቴር ማግዳሊያና አንደርሰን ራሽያ በዩክሬን ላይ ያደረገችው ወረራ ስዊድን ላለፉት 200 አመታትምንም አይነት ወታደራዊ ጥምረት ሳታደርግ የቆየውን ውሳኔ እንዳስቀየራት እና አገራቸው ከሁሉም የኔቶ አባልት ጋርእየተነጋገረች መሆኑን አስታውቀዋል።
የኔቶ አባል ለመሆኑ ከ30 የጥምረቱ አባላት ተቀባይነት ማግኘት አስፈልጋል።