ደራሼ ውስጥ የጅምላ እስር እና አፈሳ መኖሩን ነዋሪዎች ገለፁ፤ ክልሉ አስተባብሏል

Your browser doesn’t support HTML5

ደራሼ ውስጥ የጅምላ እስር እና አፈሳ መኖሩን ነዋሪዎች ገለፁ፤ ክልሉ አስተባብሏል

በደቡብ ክልል የደራሼ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የጅምላ እስር እና አፈሳ መኖሩን ገለፁ።

እስሩ የኃይማኖት አባቶች እና ሸማግሌዎችን ጨምሮ ንፁህና እና ጥፋተኛውን እንደማይለይ በመግለፅም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ቆስለው በጊዶሌ እና በአርባ ምንጭ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ የነበሩ ጉዳተኞች ጭምር መታሰራቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በወረዳው በተከሰተው የፀጥታ ችግር እጃቸውን አስገብተዋል የተባሉ 330 ተጠርጣሪዎችን ወረዳውን የተቆጣጠረው ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዙ ማሰሩን አስታውቋል።

በወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉን እንጂ በአፈሳ ያሰሩት እንደሌለም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ገለፀዋል።

“ከሕክምናቸውም አስነስተን ያሰርነው ወንጀልኛም የለም” ሲሉም አስተባብለዋል።

የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ዘገባ ልኳል።